ASTARO


Africa Asteroid Search Campaign May 17/June 30
(Team Ethiopia)
Dear students and teachers

ክቡራን ተማሪዎች እና አስታማሪ


አስትሮሜትሪካን ሶፍትዌር ለማስፈር እና ለማንቀሳቀስ (download and run) የሚከተለውን እርምጃ ውሰዱ

1) Download software   if yes go to #2
አስትሮሜትካን ያስፍሩ።፡አስትሮምሜትሪካን አስፍራው ከሆነ ወደ #2 ይሂዱ

አስትሮሜትሪካን ካላሳፈሩ

አ)፡ወደ ድረ ገጽ    http://iasc.hsutx.edu/  ይሂዱ

በ) Astrometrica (አስትሮሜትሪካ) የሚለውን ቃል  ቀጭ ቀጭ (ወይም ጫን፡ጫን) ያርጉት

ሰ) አስትሮሜትሪካ ውስጥ ያሉትን ፋይሎች በሙሉ ወደርስዎ ኮምፑተር ያስፍሩ

2) የአስትሮሜትሪካን ማሕዳር ወደ "C:\Program Files" ማኅደር ያዛውሩ:። ከዚህ በኋላ  አስትሮሜትሪካን ያንቀሳቅሱ (ምስሉን ላይ  ቀጭ ቀጭ አድርጉ። አሁን የኣስትሮሜትሪካ  መስኮት (window ወይም ሠሌዳ) ይታያችኋል። በጥሞና ተመልከቱት።

ሀ) ሠሌዳው መካከል ላይ ትንስሽ ሠሌዳ ኣለች። በነጭ አልፋቤት የተጻፈ "አስት
ሜትሪካ" የሚል ነው።  "Continue" የሚለዉን ቀጭ ቀጭ ያድርጉት።
ለ) ኮ
ቱተሩ ሥራዉን ሲጨርስ  ጢጥ ጢጥ የሚል ድምጽ ያሠማል። ሁል ጊዜ አስትሮሜትሪካ በሚንቄሳቄስቤጊዜ ይች ጢጥ ጢጥ፤ ድምጽ ትሰማለች። ትልቁ ሠሌዳ መካክል ትንሽ ሠሌዳ ኣለች። "YES" የሚለውን ቀጭ ያድርጕ
 
ሐ)አሁን ትልቁ ሥሌዳ ባዶ ነው፨

መ)
ህንን ሠሌዳ በጥሞና አጥኑት። የለይኛዉን ክፈፍ ላይ የምትመለከቷቸው የአስትሮሜትሪካን ፕሮግራም የሚያንቀሳቅሱ ትሥሥሮች (links) ናቸው።
----ለምሳሌ File የሚለውን ጫን ቢሉት ብዙ ምርጫ ያገኛሉ።  ይህ መዝገቦችን ለማስፈር(ሎድ) ወይም ለማስቀማጥ (ሴቭ ለማድረግ ) Edit የሚለውን ጫን ቢሉት እንዲሁ ሌሎች ምርጫዎች  እያለ ይቀጥላል። ከዳር እስከዳር ላይኛው ክፈፍ  ያሉት ትሥሥሮች ፕሮግራሙን ለማንቀሳቀስ የተሠሩ ናቸው። እያንዳንዱን ትሥሥር እየትጫኑ ለምን ነገር እንደተሰራ ያጥኑ

ሠ)፡አሁን ደግሞ File  Edit Astrometry Image Tools Internet Windows Help ካሉብት መሥመር በታች ያሉት ምሥሎች ራሳቸዉን የቻሉ ትሥሥሮች ናቸው።

ረ) አሁን ደግሞ የሠለዳውን ታች በስተቀኝ መጨረሻ ያለውን ክፋፍ ይመልከቱ።  የምታነቡት ARI-24.cfg ካልሆነ፤ የሚከለዉን እርምጃ ይውሰዱ

a) FILE ፈይል የሚለውን ይጫኑ፤  Settings የሚለውን ይምረጡ፤  አሁን ትልቁ ሠሌዳ መካከል አነስተኛ አዲስ ሠሌዳ ይታያል። ከዚህ ሠሌዳ CCD የሚለውን ምረጡ። ታችኛዉ ክፈፍ  Open  የሚለውን ቀጭ ያርድርጉ። አሁን አዲስ ሠሌዳ ይታያል። ሁሉ ነገር በትትክክል ከተሠራ፤ አሁን የሚያዩት ሠሌዳ configuration የሚባለው ማኅደር ነው።  ARI-23.cfg የሚባለውን መዝገብ መርጠው Open  ላይ ቀጭ ያድርጉ ። ከዚህ ቀድሞ የነበረው ሠሌዳ ብቅ ይላል። እታችኛው ክፈፍ ሄደው Save  የሚለውን ቀጭ ያድርጉ። ወድያው OK  የሚለውን ትሥሥር ቀጭ ያድርጉ።
አሁን ትልቁ ሠሌዳ ብቅ ይላል።

b)ኢንተርኔት ( internet) የሚለውን ትሥሥር ቀጭ ያድርጉ (Download MPCOrb)የሚለውን ትሥሥር ይምረጡ።  የኢንተርኔት ግንኙነት ካለ
ኮምፑተርዎ " MPCOrb" የሚባለው ማሕደር እና ዉስጡ ያሉት መዛብት ወደ አስትሮሜትሪካ ማሕደር ይቀዳሉ (copy)

c )ኣንድ ጊዜ  MPCOrb ከሰፈረ በኋላ፤ ሁለተኛ ጊዜ   አስትሮሜትሪካ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ  MPCOrb    "የአሁን" (current or upgrade) ማድረግ ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ

1)፡ኢንተርኔት ( internet) የሚለውን ትሥሥር ቀጭ ያድርጉ-update MPCOrb የሚለውን ምረጡ። ትንሽ ሠሌዳ ብቀ ትላለች።  ውስጧ አምስት ነጫጭ ካሬዎች (አራት ማዕዘነት) ይገኛሉ። እያንዳንዱን ቀጭ በማድረግ መርጠው OK የሚለው ላይ ቀጭ ያድርጉ። ከምፑተሩ ሥራውን እስከሚጨርስ ተዕግስት ይጠብቁ

========================
ሙከራዎች

1) አስትሮሜትሪካ ማሕደር ዉስጥ "Tutorials" የሚባል ማሕዳር ይ
ገኛል። እዚህ ማሕደር ብቀጥታ ሄደው፡ ዉስጡ ያሉትን መዛግብት ወደ ቆሻሻ (Trash)  ማኅደር ይውሰዱ

2) ከዚህ በፊት የላኩላችሁን መዛግብት ወደ Tutorials ማሕደር አዛውሩ።  አ
ደኛው መዝገብ "ዚፕድ" ስለሆነ  "አንዚፕ" ያድርጉ። እነዚህ መዛግብት መለማመጃ የሚሆ  ድንክዬ ፕላኔቶች ያሉቸው ፎቶግራፎች ናቸው። ዋናው ዓላማ አስትሮሜትሪካን በመተቀም እነዚህን ድንክዬ ፕላኔቶች ማግኘት
ኮምፑተር
3) አሁን ወደ "File" የሚለውን ትሥሥር ቀጭ ያድርጉ፤ "Load Images" የሚለውን ምረጡ፤  "Tutorial" የሚለውን ማሕደር ፈልገው ያግኙ ፤

የሦሥት ፎቶግራፎች መዛ
ብት ይታያሉ፤  ሦሥቱንም ምረጡ

4)፡ትናንሾች ሠሌዳዎች ባዩ ቁጥር OK የሚለውን መጫን

5) ላይኛው ክፈፍ ውስጥ ካሉት  ትሥሥር ምርጫዎች ፡ "Astrometrica" የሚለውን ቀጭ ያድርጉ እና፤ "Moving Object detection"  የሚለውን ይምረጡ።

6) አሁን ትንሽ ሠሌዳ ብቅ ትላለች። ከላይ ክፈፏ ውስጥ "Coordinates" ትላለች OK የሚለውን መርጠው በትዕግሥት ይጠባበቁ

7) አሁን ትንሽ ተንቀሳቃሽ ሠሌዳ ይታያል፤ በይህ ሠሌዳ ውስጥ ግራፍ እና  ቀይ ክብ ይታያል።

8) ይህንን ተንቀሳቃሽ ሠሌዳ በጥሞና ይመልከቱት

9) የይህንን ሠሌዳ ግርጌ ተመልከቱ። Object designation"  ሁለት ክፍት ቦታዎች እና በመካከላቸው ውስጧ ነጠብታብ ያላት ካረ  ትታያለች።  "Accept"  "Reject" የሚሉ ትሥሥሮች ወይም ትዛዞች አሉ

10) "Object designation" በሚለው ስር የጥያቄ ምልክት (?) ካለ Reject የሚለውን ቀጭ ያደርጉ

11)አሁንም ይህ ተንቀሳቃሽ ሠሌዳ ብቅ ይላል። ቅዩ ክብ ዉስጥ ነጭ ደመቅ ያለ ነገር ካዩ እና "Object designation" በሚለው ስር የተጻፈ ነገር ካለ (ለምሳሌ (39655) 1995 UM3) "Accept" የሚለውን ቀጭ ያድርጉ

12)ተንቀሳቃሹ ሠሌዳ እስከሚጠፋ ደረስ  ይህ ሂደት ይቀጥላል።

13)  እንደው ለምሳሌ ሂደቱ አለቀ እንበል። አስትሮሜትሪካ በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት ይንቀሳቅሳሉ ተብለው የሚጠረጠሩትስ ደንክዬ ፕላኔቶችን ኣጌኝቶ ጬርሷል ማለት ነው። የርስዎ ሥራ ገና መጀመሩ ነው።

14)  ከላይኛው ክፈፍ ውስጥ፤ "Tools" የሚለው ላይ ቀጭ ያድርጉ፤  "Known Object Overlay" ምረጡ

15)  ከምፑተሩ ሥራዉን እስከሚጨርስ በትዕግሥት ይጠብቁ

16) አሁን በቀያይ የ
ጻፉ በካሬ የተከበቡ ይታያሉ። ይህ  እርምጃ የሚጠቅመው በ 10ኛ  11ኛ እና 12ኛ ላይ የተገኙት ድንክዬ ፕላኔቶች ምናልባት ከታወቁት መካከል መሆን አለመሆናቸውን ለማመሳከር ነው።

17) የታወቁት እና አዲስ የተገኙት አንድ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ ፎቶግርራፎቹን አጉልቶ(zoom in) ወይም አሳንሶ (Zoom out)  ለማየት ሁለት መንገድ አለ

17a) ከላይኛው ክፈፍ "images" የሚለውን ቀጭ ያድርጉ፡ ለማጉላት  Zoom in የሚለውን ምረጡ  ለማሳነስ Zoom out የሚለውን ምረጡ

17b) እላይኛው ከፈፍ File ከሚለው በታች በመደዳ ሠዕሎች አሉ። ሁለቱ
እጄታ ያላቸውን ክቦች ተመልከቱ። አንደኛው ክብ ውስጥ የመደመር ምልክት (+)  አንደኛው ውስጥ ዳግሞ የመቀነስ ምልክት(-)  አሉ። የመደመር ምልክት ያለው ማጉሊያ ነው

18) Tools የሚለውን ትሥሥር ቀጭ ያድርጉ፤ "Blink images" አሁን ሦሥቱ ፎቶግራፎች ተራ በተረ እንደ ሲኒማ ይንቀሳቀሳሉ።

አሁን አትኩሮ ማየትና ልብ ማድረግ የሚያስፈልገው ሁለት ነገሮች ናቸው

፩ኛ) ሲኒማው ከመጀመሪአው ፎቶግራፍ ወደሚቀጥለው ሲሸሸጋገር  ድንክዬ ፕላኔ
ቹ  በቀትተኛ መሥመር እንጣጥ እንጣጥ ሲሉ ይታያሉ

፪ኛ) ከ ድንክዬ ፕላኔትቹ በስተጀርባ ያሉት ከዋክብት ግን ቦታቸውን ሳይለቁ እዛው ባሉበት ብልጭ ብልጭ ይላሉ

ወደፊት ሰፋ ያለ ማብራሪ
ይሰል፡ በዕግሥት ይጠብቁ-
Google Groups
Africa Space Science and Astronomy Network
Visit this group

Participating Schools

Ethiopia

Bishoftou Preparatory (Bishoftu)
Hawas High School (Adama)
Saint Joseph (Addis Ababa)
Adama University (Adama)
Addis Ababa University (AAU)

Schools on Standby

AASDO Schools (Assella)
Mekele Schools (Mekele)
Bahir Dar Schools (Bahir Dar)

South Africa

North Carolina Schools

Links
Space Africa

African Scientific NetworkUpdated: Mar 15, 2007