Ethiopian Binary Multiplication
  ኢትዮጵያ መደበሁለት (Base two or binary) ሒሳብ

የኢትዮጵያ ኅብረተ ሰብ ከብዙ ዓመታት በፊት ጀምሮ እስከአሁን የባህል ዕውቀታቸውን በመጠቅም ይገበያያሉ። ይህ ነባር ዕውቀት  ግዜን፤ ኤርቄትንና መጠነክብደትን፡ መጠንና ስፋትን፤ ዙሪያን የመሳሰሉትን ይለካሉ። እነዚህም ልኬቶች የሚከናውኑት ባህሉና ዘመኑ ባመጧቸው የልኬት መሣሪያዎች ነው። ለምሳሌ ግዜን ለማወቅ በባህል የጥላን ርዝመት በመለካት ግዜውን ለማወቅ ይቻላል። ይህ የመጀመሪያው ሰዓተ-ፀሐይ (sun dial) ነው (ሰንጠርጅ ፩)።

የርሻን መሬት ለመለከት ወይም ቀላድ ለመጣል ፡ ጠፍር ይጠቀማልሉ።
ለምሳሌ አንድ ጋሻ መሬት አራት ጠፍር ሲሆን፤ አንድ ኩርማን መሬት ዙሪያው አንድ ጠፍር ይሆናል። መጠነክብደት ይሚለካው በሚዛን ሲሆን ይህም ከቋሚ ክብደት ጋር በማወዳደር ነው። እህል ሲሰፈር በእንቅብ በአቁማዳ ልችርቻሮ ደግሞ በቁጭብሉ ይሆናል። ይህ ሁሉ ሲስራ ምንም ዓይነት ዘመናዊ መሳርያ ሳይስፈልግ ነው።፡ዘመናዊ መሳርያ ያሻሻለው  ገበያን በፍጥነት ለማከናውን በማስቻሉ ነው። የኢትዮጵያ ነባር ዕውቀት ለኢትዮጵያ ርምጃ ትልቅ አስተዋፆ ያደርጋል፤ ምክንያቱም ዘመናዊ ሳይንስና ሒሳብ ምርኩዛቸው ይህ ዕውቅት በመሆኑ ነው።  ይህንን ግልጽ በሆነ ምሳሌ ለማስረዳት የኢትዮጵያን ሁለት መደብ ሒሳብ በምሳሌ እናቀርባለን።

የዛሬ አንድ ሽህ ዓመት አንድ የበግ ነጋዴ 47 በጎች እያነንዳንዱን በ 17 ብር ለመሸጥ ገብያ መጣ። አሁን የአርባ ሰባቱ ብጎች ጠቅላላ ዋጋ ምን ያህል ነው ? በዘመናዊ ሒሳበመሣርያ ሁለት ሴኮንድ ባልሞላ ግዜ ውስጥ ጥቅሉን ለማወቅ ይቻላል ይህም
47 X 17 = 799  ይሆናል
የኢትዮጲያ መደበሁልትን ሒሳብ በመጠቀም ይህንን ብዜት እናሰላለን

መደብሁለትስ ሒሳብ ሥራ ላይ ለማዋል የምንከተልው ህግ
--ሁለት ጥንድ ቁጥሮች አንዱ ጎዶሎ አንዱ ሙሉ ወይመ ሁለቱም ሙሉ  ከሆኑ ከይሲ(መጥፎ ዕድል) ይባላሉ። እነዚህ ጥንዶች ከሒሳቡ ወስጥ አይገቡም

ሁለቱን ቁጥሮች በሁለት ቁመት ባለው ስንጠረጅ ማስቀመጥና ህጉን ተከትሎ ሰጠረጁን መሙላት። የሰጠርጁ አገድመቶች የሚወሰነው በሚባዙት ቁጥሮች መጠን ነው።

በ 2 አብዛ
በ 2 አካፍል
ከይሲ/ጥሩ ተደማሪ
20 x 47
47
17
ጥሩ
47
21 X 47
94
8
ክይሲ
0
22 x 47
188
4
ከይሲ
0
23x 47
376
2
ከይሲ
0
24 x 47
752
1
ጥሩ
752መልስ
799

ምሳሌ ፪፡ ዛሬ ትንሽ ጠቦት በግ 27 ብር ብታውጣና ነጋዴው 97 ብጎች ቢኖሩ፤ ጥቅሉ 97 ሲባዛ በ 27 ይሆናል። የዚህ ስሌት --

97 x 27

በ 2 አብዛ
በ 2 አካፍል
ከይሲ/ጥሩ
ተድማሪ
20 x 97 97
27
ጥሩ
97
21 x 97 194
13
ጥሩ
194
22 x 97 388
6
ከይሲ
0
23 x 97 776
3
ጥሩ
776
24 x 97 1552
1
ጥሩ
1552ደምር
2619

ይህንን የኢትዮጵያ መደበሁለት ሒሳብ   ሲጤን ግልጽ የሆኑ
የዘመናዊ ሒሳብ  ዘይቤዎችን ፈልቅቆ ለማውጣት ይቻላል።

97 X 27 = 1 x 97 + 2 x 194 + 8 x 97 +16 x 97
= (1+2+8+16) x 97 = 25 x 97 + 2 X 97


ዞሮ ዞሮ የኢትዮጵያ ሥራዓት ብዜት መደበሁለትn (binary) የሚከተል ነውሰንጠረጅ፩  ስፍረ  ሰዓት ምሳሌዎች
ወር
ስፍረ ሰዓት
እግረ ርዝመት
ታህሳስ
ዓብይ ነግህ
29

ንዑስ ነግህ
12

ዓቢይ ሰለስት
15

ማዕከላዊ ሰለስት
12

ንዑስ ሰለስት
10

ዓቢይ ቀትር
9

ማዕከላዊ ቀተር
10

ን ዑስ ቀትር
12

ዓቢይ ሰዓት
15

መዕከላዊ ሰዓት
19

ንዑስ ሰዓት
29

ሠርክ
70

ወር
ስፍረ ሰዓት
እግረ ርዝመት
ህዳርና ጥር
ዓብይ ነግህ
27.5

ንዑስ ነግህ
17.5

ዓቢይ ሰለስት
13.5

ማዕከላዊ ሰለስት
10.5

ንዑስ ሰለስት
8.5

ዓቢይ ቀትር
7.5

ማዕከላዊ ቀተር
8.5

ን ዑስ ቀትር
10.5

ዓቢይ ሰዓት
13

መዕከላዊ ሰዓት
17

ንዑስ ሰዓት
27

ሠርክ
70

ወር
ስፍረ ሰዓት
እግረ ርዝመት
ጥቅምትና የካቲት
ዓብይ ነግህ
27

ንዑስ ነግህ
17

ዓቢይ ሰለስት
12

ማዕከላዊ ሰለስት
9

ንዑስ ሰለስት
7

ዓቢይ ቀትር
6

ማዕከላዊ ቀተር
7

ን ዑስ ቀትር
9

ዓቢይ ሰዓት
12

መዕከላዊ ሰዓት
17

ንዑስ ሰዓት
27

ሠርክ
70