[ምዕራፍ አንድ ][ምዕራፍ ሁለት ][ ምዕራፍ ሦሥት ]
ወጭት-ላይሬ ከሠሜን አፍሪቃ ክራር፤ የድያብሎስ መሣርያ ተረቶች፡

Abebe Kebede (ዶ/ር አሸናፊ ከበደን በመከተል)

ምዕራፍ አንድ፤ ታሪካዊ አመጣጥ


ላይሬ ከአባይ ወንዝ አካባቢ መምጣቱን ተረቶች ያመለክታሉ። ለምሣሌ፤ የግሪኮች አንዱ ተረት  የሚለው እንዲህ ነው።፡”.. ሜርኩሪ አባይ ዳርቻ አንድ ቀን ሞታ የደረቀች ዔሊ አገኘ። የዔሊዋን ድንጋይ ተጠቅሞ ላይሬን ወጠነ'' ይላሉ።  ይህንን ጉዳይ ወደ ፊት በሁለተናውና ምዕራፍ እንመለከትና፤ በሦሥተኛው ምዕራፍ ውስጥ ስለ ክራር ወይም ስለ ላይሬ ሕብሬ ከዎክብት እናጠናለን።


ታሪካዊ ሠነዶች ላይሬ ከ፪ሽ፯መቶ ዓመተ ፍዳ በፊት በሡሜርያ በዓላት ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ እንደነበር፤ያስረዳሉ። ከዚያም አልፎ ደግሞ  ከ፪ሺ ዓመተ ፍዳ አካባቢ በተሣሉ በግብፅ ሰዕሎች የሴማዊ ዘሮች ላይሬ ይዘው ይታያሉ።  ፩ሺህ ፪መቶ ዓመተ ፍዳ (ዓመተ ምህረት ከመጀመሩ በፊት) በፊት ከአስያ ወደ ሠሜን እና ሠሜን ምሥራቅ አፍሪቃ ከፍተኛ ዓፀታት ነበሩ። በነዚህ ዓፀታት ሳቢያ ላይሬ እና የምእራብ አስያ በገና የመሣሠሉ አዳዲስ የሙዚቃ መሣሪያዎች ብቅ ብቅ ማለታቸው ይገመታል። የአስያ ላይሬ ዓይነተኛ የሚያደርገው ዓንፃራዊንተ  አራት ማዕዘን ቅርፅ ኖሮት ሁለት ትትይዩ እጆች እና እነርሱን የሚያያዝ አግድሞሽ አሉት። ባሁኑ ግዜ ትስፋፍቶ ከሚገኘው የምሥራቅ አፍሪቃ ላይሬ  የድምጽ ማውጫው ሳጥን ወይም አታሞ ክብ ሲሆን፡የአስያ ላይሬ ግን የግሪኮችን  ኪታራ እና የኢትዮጵያን በገና ይመስላል።  የዕብራውያን ላይሬዎች አባይ ሸለቆ በተለይ ኢትዮጵያ ከሚገኙት ጋር አምሣያ አላቸው። እነዚህ ትናንሽ፤ ሦሥት ማዕዘን እና አታሟቸው እንደ ድስት ክብ ናቸው። የኢትዮጵያ እና የዕብራውያን ላይሬዎች ተግባራዊ ተመሣሣይነት አላቸው። ዕብራውያን በባቢሎን ስደት ግዜ ላይሬ ወይም ኪኖር (ክራር)  መጫወት ተከልክለው ነበር። ይህ የተደረገበት ምክንያት ኪኖር (ክራር)  የደስታ እና የኅጥያት ምልክት ተብሎ ስለሚታመን ነው።
ይህ ታሪክ የሚቀትለውን ታዋቂነት ያለውን ዘፈን ያስታውሰናል።
By the rivers of Babylon,
There we sat down, yea, we wept,
When we remembered Zion.
Upon the willows in the midst thereof
We hanged up our harps.1
በባቢሎን ወንዞች ዳር
ተቀምን አለቀስን
ጽዮንን ስናስታውስ
ላይሬችንን እንጨት ላይ ሰቀልን

ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ ኢትዮጵያ  ከሜዴትራንያ እና በአዋሳኝ የአፍሪቃ አገሮች የባሕል ግንኙነት ነበራት። በዚህ ምክንያት ለይሬን ጨምሮ ተመሣሣይ የሙዚቃ መሣሪዎች በነዚህ ሐገራት ተስራጭተው ይገኛሉ።
በአባይ በስተ ምሥራቅ ሐገሮች ውስጥ የሚገኘው ላይሬ   የኢትዮጵያን ክራር ይመሥላል። ነገር ግን ይህ ላይሬ  ብርኩማ የለውም። ጅማቶቹ የሚገኙት በድምጽ ማጉያ አታሞው ላይ ነው። ላይሬው ሲመታ ወይም በጣት ሲቆነጠር ወይም ሲቆነጠር ተረም ተረም ነዘር ነዘር የሚል ድምጽ ይሰጣል።

ለምሣሌ የዩጋንዳ ላይሬ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ክራር ክሮቹን በጣት ሲቆነጥሩት ድምጽ ይሰጣል። የዩጋንዳ ልክ እንደ ሱዳን ላይሬ ክቡን የድምጽ ማጉያ በመጠቀም ይቃኛል። የኢትዮጵያ ክራር ግን እራሱን የቻለ ከቀጫጭን እንጨት የተሠሩ መቃኛዎች አሉት። በተጨማሪ ልክ እንደ ግሪክ እና ዕብራዊ ላይሬ  ክራር በጣት እያተቆነጠረ ወይም በመምቻ እየተቧጠጠ መጫወት ይቻላል። ሱዳንም እንደዚሁ ነው። ለምሣሌ ላይሬ አመጣጡ ከዓረቦች ነው። በተለይ በኑቢ እና መረውቲክ ዘመነ መንግሥታት ግዜ የነበሩ ድንጋይ ላይ የተሣሉ ምሥሎች እንደሚያሳዩት በዚያን ግዜ ሙዚቀኞች እስክስታ ወራጆች በገናን ወይም ላይሬ ተጠቅመውበታል።

በኢትዮጵያ ግን የሙዚቃ መሣርያ አጠቃቀምን እና ዓይነትን  እንደዚህ ዓይነት ማሥረጃ አልተገኘም። የሆነው ሆኖ ኢትዮጵያ እና አቅራቢያ ሐገራት በአማካይ ያላቸው ታሪክ ስለሚታወቅ የላይሬን ጥቅምና አመጣጥ ማረጋገጥ ይቻላል።

ምዕራፍ ሁለት፤
ክራር የዲያብሎስ መሣሪያ ለምን ተባለ?

ምዕራፍ ሦሥት፤
የክራር ወይም የላይሬ ሕብረ ክዋክብት ምን ይመስላል ?